ፋኖን እቀጣለሁ በሚል መሰረታዊ አገልግሎቶችን ከልክሎ መላውን የአማራ ህዝብ መቅጣት የጦር ወንጀልና መንግሥታዊ ሽብርተኝነት ነው

 ethiopian human right commussion
October 2023

by voice of fano

ፋኖን እቀጣለሁ በሚል መሰረታዊ አገልግሎቶችን ከልክሎ መላውን የአማራ ህዝብ መቅጣት የጦር ወንጀልና መንግሥታዊ ሽብርተኝነት ነው። ፋኖ እስካሁን በንጽኋን ዜጎች ላይ ጥቃት መፈጸሙንና በሽብርተኝነት የሚያስፈርጀው አንዳች ማስረጃ ፈልጎ ማግኘት አይቻልም። የአብይን መንግሥት በመንግስታዊ ሽብርተኝነት (state terrorism) የሚያስወነጅለውን አንድ ሺ አንድ ማስረጃዎችን ግን ማቅረብ ይቻላል። የአማራ ህዝብ አገልግሎት ሲያጣ አሜን ብሎ ይገዛል የሚለው እሳቤ የህዝቡን ስነልቦናና ታሪክ ካለማወቅ የሚመነጭ ነው።

ይህ ስትራቴጂ የገዢዎችን ወንጀል ከመከመር ውጭ የሚፈይደው አንዳች ነገር የለም። ሁሉም ጦርነቶች በህግ መገዛት አለባቸው። አሁን እንደምናየው ግን "ኤሊት" እየተባለ ከሚቆለጳጰሰው የመንግሥት ሰራዊት ይልቅ፣ በቂ ወታደራዊ ትምህርት የሌለው ፋኖ በተሻለ ሁኔታ የጦር ህግ አክብሮ እየተጓዘ ነው። አሁንም የአማራ ህዝብ መሰረታዊ አገልግሎት እንዲያገኝ እንጠይቃለን። ግብር የሚከፍለው ለባለስልጣናቱ ቪ8 መኪናና ሱፍ አይደለም።

ጋዜጠኛ ፋሲል የኔዓለም